እኛ የቆምነው


የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የስራ እድል ፈጠራ ኮሚሽን የፌዴራል መንግስት ስራ አስፈጻሚ አካላት ስልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 1097/2011 መሰረት የተቋቋመ ሲሆን ይህንን ተከትሎ የኮሚሽኑን ተግባር፣ ሃላፊነት እንዲሁም አደረጃጀት ለመወሰን በሚኒስትሮች ምክር ቤት ባጸደቀው ደንብ ቁጥር 435/2011 መሰረት ብሄራዊ የስራ ፈጠራ አጀንዳውን የመምራት፣ ባለድርሻ አካላትን የማቀናጀት እንዲሁም አፈጻጸምን የመከታተል እና የመደገፍ ስልጣን ተሰቶታል፡፡

የሀገሪቱን የስራ ዕድል ፈጠራ በአዳዲስ የፈጠራ ሀሳቦች፣ በቅንጅት እና በተግባር በመምራት

ሁሉም ዘላቂ ሥራ የሚያገኝባት ሃገር ሆና ማየት

ፈጠራ
ልቀት
ትብብር
ባለቤትነት

የኮሚሽኑ መዋቅር


ምክትል ኮሚሽነር የፖሊሲና ስትራቴጂ ዳይሬክቶሬት የግዥ ንብረት አስተዳደርና የሠዉ ኃብት ዳይሬክቶሬት የሥራ ዕድል ፈጠራ ክትትል እና አቅም ግንባታ ዳይሬክቶሬት አዳዲስ የሥራ ዕድል ፈጠራ ፕሮጄክቶች ዳይሬክቶሬት የትብብር እና ኢንቨስትመንት ዳይሬክቶሬት የግዥ ንብረት አስተዳደርና የሠዉ ኃብት ዳይሬክቶሬት ኮሚሽነር Commissioners የኮሚሽነር /ቤት

የሥራ ክፍል መሪዎች


ኮሚሽነር

ኤፍሬም ተክሌ ሌማንጎየሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን ኮሚሽነር


ዶ/ር ኤፍሬም ተክሌ የሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው በማገልገል ላይ ይገኛሉ፡፡ ወደዚህ የሥራ መደብ ከመምጣታቸው በፊት የአፍሪካ ሃገሮች መሠረታዊ የጤና አገልግሎታቸውን እንዲያጠናክሩ ድጋፍ ለሚሰጠው ዓለም አቀፍ መሠረታዊ ጤና እንክብካቤ እንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ሆነው አገልግለዋል፡፡ በተጨማሪም በሀርቫርድ ዩኒቨርስቲ የሕብረተሠብ ጤና ት/ቤት የመሠረታዊ ጤና እንክብካቤ እና የማህበረሰብ ጤና ስርዓት ተመራማሪ ሆነው ሰርተዋል፡፡

በሃገር ውስጥ በፌደራል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የእናቶች፣ ሕፃናት እና ስርዓት ምግብ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በመሆን ያገለገሉ ሲሆን በመቀሌ ዩኒቨርስቲ በምርምር እና ትምህርት መስኮችም በተለያዩ የሃላፊነት ደረጃዎች ሰርተዋል፡፡

ዶ/ር ኤፍሬም በከፍተኛ ትምህርት፣ በጤና እና በወጣቶች ልማት ጉዳይ ላይ ባተኮሩ ስትራቴጂዎችና ፕሮግራሞች ዝግጅት እና ትግበራ በመምራት ከአስር ዓመት በላይ ልምድ አካብተዋል፡፡

ዶ/ር ኤፍሬም የህክምና ዶክትሬት ዲግሪአቸዉን ከአዲስ አባባ ዩንቨርስቲ ህክምና ሳይንስ ኮሌጅ፤ በጤና አመራር እቅድና ፖሊሲ ዝግጅት የማስተርስ ዲግሪ ከሊድስ ዩንቨርስቲ እንዲሁም በህክምና ትምህርት አሰጣጥ የድህረምረቃ ሰርቲፊኬት ከካርዲፍ ዩኒቨርስቲ አግኝተዋል፡፡