ቡድን


ዳይሬክተር

ጥዑመዝጊ በርኼ ፍቃዱትብብር እና ኢንቨስትመንት ዳይሬክቶሬት


አቶ ጥዑመዝጊ በርሄ የሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን ትብብር እና ኢንቨስትመንት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሆነዉ በማገልገል ላይ ይገኛሉ፡፡ በፌደራል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የፕሮጄክት ትግበራ መምሪያ ኃላፊ እንዲሁም ወደዚህ ኃላፊነታቸዉ ከመዛወራቸዉ ቀደም ብሎ በሚኒስቴሩ ፕሮጄክት ትግበራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሆነዉ አገልግለዋል፡፡ በተጨማሪም በሚኒስቴር መ/ቤቱ የከተሞች መልካም አስተዳደርና አቅም ግንባታ ቢሮ ሃላፊ፣ የፖሊሲና ፕሮገራም ቢሮ ኃላፊ በመሆን አገልግለዋል፡፡ በዚህም ከተሞች በመሠረተ ልማት አቅርቦትና ማስፋፊያ ፕሮጀክት (ULGDP) ውጤታማ ስራ በመስራት እንዲሁም የከተሞችን የማስፈፀም አቅም በመገንባት በኩል የራሳቸውን የአመራርነት ሚና የተጫወቱ ሲሆን በከተሞች ዕድገት ላይ የራሳቸውን አስተዋፅኦ አድርገዋል፡፡

አቶ ጥዑመዝጊ በከተማ ልማት ፕሮጄክት አፈጻጸም፣ በፋይናስ ስራ አመራር እና ግዥ አስተዳደር ከፍተኛ ልምድ አካብተዋል፡፡ የስራ አመራር የሞያ ፈቃድም ባለቤት ናቸው፡፡

አቶ ጥዑመዝጊ በሂሳብ መዝገብ አያያዝ የመጀመሪያ ዲግሪ፣በፋይናነስ ስራ አመራር የድህረ ምረቃ ዲፕሎማ (Post graduate on Financial management) እንዲሁም በከተማ ልማት አስተዳደር የማስተርስ ዲግሪ ከሲቪል ሰርቪስ ዩንቨርስቲ አላቸዉ፡፡