ትስስር ለመፍጠር


ስለ ኢተርፕሬነሮች የልምድ ልውውጥ መድረኮች ለማወቅ ለምትፈልጉ ቀጥሎ የተመለከቱትን ድርጅቶች ድረ-ገጽ ማየት ይቻላል፡፡

መላ ወርሃዊ

መላ በየወሩ በሚያዘጋጀዉ ስብሰባ እንዲሁም በድረ-ገጽ መድረክ አማካኝነት በተለያዩ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፐሬነሮችንና የቢዝነስ ሰዎችን በማገናኘት ሃሳብ እንዲለዋወጡና ስለኢትዮጵያ የቢዝነስ ጉዳይ እንዲወያዩ የሚያመቻች መድረክ ነው፡፡

ድረ-ገፅ

ኢኮ ሲስተም 101


በብሉ ሙን የሚዘጋጀው ኢኮሲስተም 101 በየሁለት ሳምንቱ አነቃቂ ተናጋሪዎች የሚመሩት የልምድ ልውውጥ መድረኮችን ያመቻቻል፡፡

ድረ-ገፅ

ኢንተርፕሬነር ማይንድሴት

በኤክስ ሃብ የሚዘጋጀው ይህ ወርሃዊ መድረክ በራስ ጥረት ውጤታማ የሆኑ ኢንተርፕሬነሮች ስለልምዳቸው ትምህርት ያጋራሉ፤ ስለሚያጋጥሙአቸው ተግዳሮቶች እና መፍትሄዎቻቸው ውይይት ያደርጋሉ፡፡ የዚህ ውይይት መድረክ ተሳታፊዎች የመፍትሄ ሃሳባቸውን ውጥን በጽሁፍ በማቅረብ እንዲሳተፉ እድል ይሰጣቸዋል/ይበረታታሉ፡፡

ድረ-ገፅ