ለስራ ይመዝገቡ


የሪፖርተር ጋዜጣ ክፍት የሥራ ቦታ ማስታወቂያ ከሚያወጡ ጋዜጦች መካከል መሪ እንደሆን ይታወቃል። በተለይ በዕሮብ እትም። ኢትዮ ጆብስ የዲጂታል ክፍት የሥራ ቦታ ማስታወቂያ መሪ ድረገፅ ነው። ለተጨማሪ የክፍት የሥራ ቦታ ማስታወቂያ ድረገፆችን ለማግኘት ከታች የሚገኙትን ሊንኮች ይመልከቱ።

ሥራ በመፈለግ ሂደት እንዲሁም ለሥራ መስክ እድገት ጠቃሚ ምክሮች


የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮን ይጎብኙ

ተማሪዎች በዩኒቨርስቲያችሁ ወይም አቅራቢያ የሚገኙ የሥራ ማዕከሎችን ጎብኙ

ሥራ ፈላጊዎች ለቃለ መጠይቅ በምታደረጉት ዝግጅት ማስታወስ ያለባችሁ


ለቃለ መጠይቅ በምታደርጉት ዝግጅት፤

በቃለመጠይቅ ወቅት አዘውትረው የሚጠየቁ ጥያቄዎችን በመለየት በነሱ ላይ ዝግጅት ማድረግ፣
ለቃለመጠይቅ ስለጠራችሁ ድርጅት መረጃ በማሰባሰብ ስለድርጅቱ በቂ ግንዛቤ መያዝ ይገባል፣
ቃለመጠይቁ ወደሚደረግበት ቦታ በግዜ መድረስ፤ ዘና ብሎ መጠበቅ፣
በዚህ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃ ቢያስፈልግ የሚከተሉትን ድረ-ገጾች መጎብኘት ይቻላል፡፡
EthioJobs
Livecareer

ለሲ.ቪ ዝግጅት

ሲ.ቪ. አንድ ሥራ ፈላጊ ስለ ራሱ የግል መረጃ፣ ስለ ትምህርት ደረጃውና ሥራ ልምዱ የሚያቀርበው መግለጫ ነው፡፡ በሲ.ቪ ዝግጅት ወቅት ቀጥሎ ያሉትን ነጥቦች አስታውሱ፤


በቀላሉ የሚነበቡ ፊደላትና የገጽ አደረጃጀት ተጠቀሙ
የሰዋሰው እና ሌሎች ግድፈቶች እንዳይኖሩ ጥንቃቄ አድርጉ
የሚቀርቡ መረጃዎች የቅርብ ጊዜ መሆን አለባቸው
በዚህ ጉዳይ ላይ ተጨማሪ መረጃ ቢያስፈልግ ቀጥሎ የተመለከቱትን ድረ-ገጾች መጎብኘት ይጠቅማነል
EthioJobs
Oxford Dictionary
Standout
Resuming

ስልጠናዎችየቴክኒክ እና ሙያ ትምህርትና ስልጠና


01

መደበኛ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና


ከደረጃ 1-5 ባለው ለመሰልጠን ከ10-12ኛ መደበኛ ትምህርት ማጠናቀቅ

131,097


በ2016 የቴክኒክና ሙያ ስልጠና አጠናቀው የተመረቁ

86%


ያህል ተማሪዎች በመንግስት የቴክኒከና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት ይማራሉ

ተደራሽነት

የደረጃ 1-5 ስልጠናዎች መግቢያ በ10ኛ እና 12ኛ ብሔራዊ ፈተና ውጤት መሰረት በትምህርት ሚኒስቴር የሚወሰን ነው፡፡


በተወሰነው የመግቢያ ውጤት መሠረት ሥልጠናውን መከታተል መቻል አለመቻላችሁን ካረጋገጣችሁ በኋላ በአቅራቢያችሁ ወደሚገኝ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ት/ቤት በመሄድ በምትፈልጉት ትምህርት መስክ ለመሠልጠን መመዝገብ ትችላላችሁ፡፡

የሥልጠና መርሃ ግብሮች

የመንግስትና መንግስታዊ ያልሆኑ የሥልጠና ተቋማት የቀንም ሆነ የማታ ሥልጠና ይሰጣሉ፡፡


የሥልጠና መርሃግብሮች እስከ ሶስት ዓመት ሊወስዱ ይችላሉ፡፡


ሠልጣኞች ትምህርታቸውን ካጠናቀቁ በኋላ የብቃት ማረጋገጫ ፈተና (COC) እንዲወስዱ ይጠበቃል፡፡ ያንድአንድ የሥልጠና መስኮች ሰልጣኞች COC ፈተና ላይወስዱ ይችላሉ፡፡

ስርዓተ-ትምህርት

የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ሥርዓተ ትምህርት የሥልጠና መስኩን ቴክኒካዊ ዕውቀት ፣ የኢንተርፕሬነርሽፕ ትምህርትና የካይዘን ኮርሶችን ያካተተ ነው፡፡


የሥልጠናው 70 በመቶ ተግባራዊ ትምህርትን የሚሸፍን ሲሆን ይህም በትምህርት ቤቶች ውስጥ በሚደረግ ልምምድ እና ሰልጣኞች በየድርጅቶች ውስጥ ተመድበዉ በመሥራት በሚያገኙት የተግባር ልምምድ (አፓረንተሽፕ) ይከናወናል፡፡


የቴክኒክና የሙያ ትምህርት ቤቶች ፌደራል የቴክኒክና ሙያ ኤጀንሲ በሚያወጣው የሙያ ደረጃ ላይ ተመስርተው የራሳቸውን ስርዓተ ትምህርት ያዘጋጃሉ፡፡

ለቴክኒክና ሙያ ምሩቃን ያሉ የሥራ ዕድሎች


በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ

ጨርቃጨርቅና አልባሳት


ቆዳና የቆዳ ውጤቶች


ምግብና መጠጥ ዝግጅት


ብረታ ብረት ሥራና ኢንጂነሪንግ


የዕንጨት ሥራ


ባህላዊ እቃዎችና ጌጣጌጦች


የግብርና ውጤቶች ማቀነባበሪያ


የኮንስትራክሽን ግብዓቶች ማምረት

በኮንስትራክሽን ዘርፍ

ግንባታ ንዑስ- ኮንትራክተርነት


ኮብልስቶን ሥራ


በመሠረተ ልማት ግንባታ


በንዑስ ኮንትራክተርነት

በንግድ ዘርፍ

የሀገር ውስጥ ምርት ጅምላ ንግድ


የሀገር ውስጥ ምርት ችርቻሮ ንግድ


የጥሬ እቃ አቅርቦት

በአገልግሎት ዘርፍ

የገጠርና አነስተኛ የትራንስፖርት አገልግሎት


ካፍቴሪያና ምግብ ቤት


የመጋዘን አገልግሎት


የቱሪስት አገልግሎት


የማኔጅመንት አገልግሎት


እቃ የማሸግ አገልግሎት


የማዘጋጃ አገልግሎት


የከተማ ግብርና

ዘመናዊ እንስሳት እርባታ


የፕሮጀክት ምህንድስና አገልግሎት


የዕቃ ንድፍና ፋብሪካ አገልግሎት


የአትክልትና ገጸ-ጊቢ ማስዋብ አገልግሎት


የጥበቃና ጽዳት አገልግሎት


የጥገና አገልግሎት


የውበት ሳሎን


የኤሌክትሮኒክስና ሶፍትዌር ማዳበር አገልግሎት

ዶሮ እርባታ


ንብ እርባታ


ዘመናዊ ደን ልማት


አትክልትና ፍራፍሬ


ዘመናዊ መስኖ


የማስዋብ አገልግሎት


ኢንተርኔት ካፌ


ጋራዥና መገጣጠም ሥራ

02

መደበኛ ያልሆነ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና


ማንኛውም ሰው ሊከታተላቸው የሚችሉ 1-3 ወር ስልጠናዎች ናቸው

975,774


በ2017 መደበኛ ያልሆነ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና የተከታተሉ ሰልጣኞች ብዛት

መደበኛ ያልሆነ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና


የመንግስትና መንግስታዊ ያልሆኑ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት ከ1-3 ወር የሚወስዱ ምንም አይነት የቅድመ ትምህርት መመዘኛ ሳያስፈልግ አጫጭር ስልጠናዎች ይሰጣሉ፡፡

አጫጭር ስልጠናዎች

በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ፣ በግል ዘርፍ፣ በልማት አጋሮች እና መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች የሚሰጡ በቀናት ውስጥ ወይም በተወሰነ ወራት የሚጠናቀቁ ጠቅላላ ወይም ሙያ ተኮር የቴክኒክና ሙያ ስልጠናዎች ይሰጣሉ፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ የበለጠ መረጃ ከEthiojobs.net ወይም dereja.com ድረ-ገጽ ማግኘት ይቻላል፡፡ በተጨማሪም የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂና የንግድ ስልጠናዎችን በተመለከተ ገበያ እና ጎበዜን መጎብኘት ይቻላል፡፡

ለኢንተርፕሬነሮችና ሥራፈላጊዎች ስልጠና የሚሰጡ ድርጅቶች

ገበያ ታለንት

ለIT ሙያተኞች በኮዲንግ እና የኮምፒውተር ፕሮግራም ዝግጅት ፣ መተግበሪያዎችንና ድረ-ገጾችን በማዳበር፣ በግራፊክ ዲዛይን ወዘተ ስልጠና ይሰጣል፡፡
ድረ-ገፅ

ጎበዜ

ጎበዝ በአጭር ጊዜ ሥራ ሊያስገቡ የሚችሉ ክህሎቶችን የሚያስታጥቁ አጫጭር የስልጠና ኮርሶች የሚሰጥ አማካሪ ድርጅት ነው፡፡ የሚሰጣቸው የስልጠና መስኮች ቢዝነስ ማበልፀግ፣ ሽያጭ ፣ የሙያ ማዳበሪያ ፣ የኮምፒውተር ፕሮግራም/ኮድ ዝግጅት ማሕበራዊ ሚዲያ ወዘተ ያካትታሉ፡፡
መሀበራዊ ድረ-ገፅ