ኢንኩቤተሮችየፋይናነስድጋፍ ሰጪዎች


ስራ መጀመር እንደትችሉ ሊረዷችሁ የሚችሉ ኢንኩቤተሮቸ አዲስ አበባ ውስጥ ይገኛሉ፡፡ ለበለጠ መረጃ ድረ-ገጾቻቸውን ጎብኙ፡፡

አይ.ሲ.ቲ.ፓርክ

200 ሄክታር ላይ ያረፈዉ አይ.ሲ.ቲ. ፓርክ አዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ከቦሌ አለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ጀርባ ይገኛል፡፡ የመሥሪያ ቦታን ጨምሮ ፈጣን የኢንተርኔት አገልግሎት፣ በቂ የኤሌክትሪከ ኃይል አቅርቦት፣ አስተማማኝ የዳታ ደህንነት፣ መሬት በተመጣጣኝ ዋጋ እና ተያያዥ አገልግሎቶችን በተጨማሪም የተለያዩ ማበረታቻዎችን ያቀርባል፡፡ የገንዘብና የፋይናንስ አገልግሎቶችን ጨምሮ የአንድ መስኮት የመንግስት አገልግሎቶች የሚሠጡ ተቋማት ይገኛሉ፡፡ እስከአሁን ከ70 በላይ የኢ.ኮ.ቴ ኩባንያዎች ወደ ፓርኩ ገብተዋል፡፡

አይስአዲስ

በ2011 የተቋቋመው አይስአዲስ ለጀማሪ የኢ.ኮ.ቴ ኢንተርፕራይዞች ስልጠና እና የጋራ መስሪያ ቦታ ያማቻቻል፡፡

ድረ-ገፅ

ብሉ ሙን

ብሉ ሙን በ2017 የተመሠረተ ኢንኩቤተር ሲሆን በዓመት ሁለት ጊዜ በሚያደርገው ሀገርዓቀፍ ውድድር የሚደግፋቸውን ጀማሪ ኢንተርፕራይዞችን ይመርጣል፡፡ የተመረጡ ጀማሪዎች ስልጠና፣ የቢዝነስ ማበልጸፀጊያ ድጋፍ፣ የመሥሪያ ቦታ፣ እና የገንዘብ ድጋፍ የሚያገኙበት ሁኔታ ይመቻችላቸዋል፡፡

ድረ-ገፅ

ዘ ኤስክ ሀብ

በአፍሪካ የአመራር ጥናት ማዕከል በ2014 የተጀመረው ይህ ኢንኩቤተር ጀማሪ ኢንተርፕሬነሮች ኃሳባውን ወደ ተጨባጭ ቢስነሶችና አገልግሎቶች እንዲያሸጋግሩ ያማክራል፣ ይድግፋል ፡፡ ይኼንንም ለማሳካት የሥልጠና እና የጋራ መስሪያ ቦታ ያቀርባል፡፡

ድረ-ገፅ

የፋይናንስ ድጋፍ የሚሰጡ ተቋማት


ለጀማሪዎች የመነሻ ካፒታል የሚሠጡ ድርጅቶች

ሪኒው

ሪኒው በታዳሽ ሃይል፣ ግብርና ውጤቶች ማቀነባባር፣ ማኑፋክቸሪንግና ጤናን ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎ የመዋዕለ ነዋይ ፈሰስ ያደርጋል፡፡

ድርጅቱ ለማስፋፊያ ከ300 ሺ - 3ሚሊዮን ዶላር ካፒታል ከፍተኛ የማደግ አቅም ላላቸው የሀገር ውስጥ ኩባኒያዎች የእንቨስትመንት ካፒታል ይሰጣል፡፡ መነሻ የካፒታል የተሰጣቸዉ ድርጅቶች ከ3-7 ዓ መት ውስጥ ራሳቸውን ከቻሉ በኋላ የድጋፍ አቅራቢውን ድርጅት የባለቤትነት ድርሻ እንዲገዙ ተደርጎ ሪኒው የባለቤትነት ድርሳን በሙሉ በሙሉ ያስረክባል፡፡
ድረ-ገፅ

ግሮውዝ አፍሪካ

ለጀማሪ ድርጅቶች የኢንተርፕሬነርሽፕ፣ የቢዝነስ ማበልፀጊያ፣ የአመራር ስልጠና እና የመነሻ ካፒታል ያቀርባል፡፡ የጀማሪዎችን እድገት ማፋጠን፣ የሀገር ውስጥና አለምዓቀፍ ኩባኒያዎች አፍሪካ ውስጥ የሚሰሩትን ስራ እንዲያስፋፉ ድጋፍ መስጠት የዚህ ድርጅት ተልዕኮ ነው፡፡
ድረ-ገፅ

ኖቫስታር ቬንቸርስ

ኖቫስተር ከፍተኛ ተስጥኦ ያላቸውን የቀጣይ ትውልድ አፍሪካዊ ኢንተርፕሬነሮች በማፈላለግ ለአፍሪካ ህዝብ አትራፊ አገልግሎት እንዲሰጡ አዳዲስ የቢዝነስ አሠራር ሞዴሎቸን እንዲያዘጋጁ እና እንዲከውኑ ይደግፋል፡፡

ድረ-ገፅ

ኢግናይት ኢንቨስትመንት

የኢንተርፕሬነርሽፕ፣ ቢዝነስ ማበልፀግ እና የአመራር ስልጠና ይሰጣል፤ ለጀማሪ ድርጅቶች የመነሻ ካፒታል ድጋፍ ያቀርባል፡፡ የጀማሪዎችን እድገት ማፋጠን ፣ የሀገር ውስጥና አለምቀፍ ኩባኒያዎች በአፍሪካ ውስጥ የሚሠሩትን ሥራ እንዲያስፋፉ መደገፍ የዚህ ድርጅት ተልዕኮ ነው፡፡
ድረ-ገፅ