በክቡር ኮሚሽነር አቶ ንጉሱ የሚመራ ቡድን በድሬደዋ ከተማ አስተዳደር፣ በሐረሪ፣ በሲዳማ፣ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች፣ ሶማሌ፣ ጋምቤላ እና አማራ ክልሎች በመገኘት የክትትልና ድጋፍ ጉብኝቶች አካሂዷል።

እነኝህ ጉብኝቶች በተለያዩ ጊዜያት የሚደረጉ ሲሆን በተለይም በመጀመሪያው ሩብ ዓመት መካሄዳቸው የክልልና የዘርፉ አመራሮች የበጀት ዓመቱን እቅድ ወደ ትግበራ የሚቀይሩበትና ከባለፈው ዓመት የተሻለ አፈጻጸም ለማስመዝገብ የሚያስችል የዝግጅት ስራዎች የሚከውኑበት ወቅት በመሆኑ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንደሚኖረው ይታመናል።

በጉብኝቶቹ ወቅት የሚደረጉት ውይይቶች ዋና አላማ በአገር አቀፍ ደረጃ የተያዘውን እቅድ ከክልሎች ጋር ለማናበብና የክልሎችና የዘርፉ ከፍተኛ አመራሮች በባለቤትነት ወስደው የየክልሎቻቸው ጸጋ በመለየትና ያላቸውን ኃብት በዘርፍ በመተንተን ለወጣቶች የስራ ዕድሎችን የማመቻቸት ስራን እንዲሰሩ ያግዛቸዋል። በመድረኮቹ ላይ የሚነሱት ጥያቄዎችና ኃሳቦች በግብዓትነት እየተወሰዱ፣ ምላሽ የሚያስፈልጋቸው ደግሞ ምላሽ የተሰጠባቸው ሲሆን የዘርፉ አመራሮችም ጉዳዩን በምክር ቤት ስብሰባዎች ላይ አጀንዳ በማድረግ ማንሳትና የሁሉም አካላት ጉዳይ መሆኑን ማስጨበጥ እንዳለባቸው አቅጣጫ ተሰጥቷል።

ከአመራሮች ጋር ከተደረጉት የምክክር መድረኮች በተጨማሪ በሁሉም ጉዞዎች የአንድ ማዕከል አገልግሎት ተቋማትና ልዩ ልዩ ኢንተርፕራይዞች ጉብኝት የተደረገ ሲሆን ይህም ከመስሪያ ቤቶች በተጨማሪ በተጨባጭ ከማኅበረሰቡ ጋር እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ያሉበት የጥራትና የተደራሽነት ደረጃ ለመገምገም እንዲሁም ቀጣይ የድጋፍ አቅጣጫዎችን ለማስቀመጥ በግብዓትነት የሚጠቅም ይሆናል።

ለክትትልና ድጋፍ ስራዎች ከፍተኛ ትኩረት መሰጠቱ በሁሉም ክልሎችና ባለድርሻ አካላት መሪነት የሚሰራውን የስራ ዕድል ፈጠራ አጀንዳ ውጤታማ ለማድረግና አገራዊ ፋይዳውንም ለማሳደግ እንደሚጠቅም ታምኖበት በቀጣይ የሩብ ዓመትም በሌሎች ክልሎች ተመሳሳይ ጉብኝቶች ይደረጋሉ።

ያጋሩት