የጃኔት ታሪክ

“ለጀማሪ ስራ ፈጣሪነት የአዕምሮ ዝግጁነት ያስፈልጋል !”

የስራ ፈጣሪነት ጉዞ በጣም ፈታኝ እንደሆነ አይቼዋለሁ፡፡ ቀላል መንገድ አይደለም! በተለይ ለጀማሪ ስራ ፈጣሪዎች ማለት የምፈልገው ነገር የአዕምሮ ዝግጁነት ያስፈልጋል ነው፡፡ ምክንያቱም ጀማሪ ስራ ፈጣሪ ሲኮን የሚፈለገው ነገር ሁሉ ተሟልቶ አይኖርም፡፡ ብዙ የሚገድቡ ነገሮች ይኖራሉ፡፡ የቢዝነሱ ፈጣሪም፣ ሽያጭ ባለሞያም ፣ የፋይናንስ ባለሞያም መሆን ሊያስፈልግ ይችላል የስራ ፈጣሪነት መንገድ ቀላል እንዳልሆነ እና የአዕምሮ ዝግጁነት እንደሚያስፈልግ መታወቅ አለበት፡፡ማንም ሰው በፈጠራ ችሎታው ወይም ልዩ በመሆኑ ማፈርም ሆነ ከመስራት ወደ ኋላ መቅረት የለበትም፡፡


ለማንበብ ይጫኑ
የሰምሃል ታሪክ

“በእኛ ሀገር ሁኔታ ወጣትና ሴት ተኾኖ ስራ ፈጣሪነት ቀላል አይደለም”

የማምረቻ ኢንዱስትሪው በብዛት በወንዶች የተያዘ ነው፡፡ ወጣት ሲኾን ደግሞ እንደልብ ከባንክ ብድር የማግኘት እድሉ ጠባብ ነው፡፡ ከምንም በላይ ደግሞ በዘርፉ ቀድሞ የገባ/ች ወይም በስራው በደምብ ልምድ ያዳበረ/ች መካሪ ከሌለ ጉዞው የበለጠ ፈታኝ ይሆናል፡፡ የእኛ ድርጅት ከአረብ ሀገር የተመለሱና በተለያዩ የሴቶች ማህበራት ስር ባሉ መጠለያዎች ውስጥ የሚገኙ ሴቶችን እና አካል ጉዳተኞችን በመውሰድ አሰልጥኖ ይቀጥራል፡፡ እስካሁን ከቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት ጋር በትብብር እየሰራን ነው። ከሰራተኞቻችን 80% ሴቶች ሲሆኑ ከእነዚህ 20% ልጆቻቸውን ያለአባት የሚያሳድጉ እናቶች ናቸው፡፡ እንደ ሴትነቴ ብዙ ሴቶችን መጥቀም እችላለሁ ብዬ አምናለሁ ፡፡


ለማንበብ ይጫኑ